በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን መኪናዎች በጥራትና በብቃት ለማቅረብ ልምድ፡ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኬኢኮአመኬፋ 010/2018
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን መኪናዎች በጥራትና በብቃት ለማቅረብ ልምድ፡ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ብዛት ሁለት መኪናዎች ሎት 1፡- አንድ ደብል ፒካፕ መኪና ሎት 2 እንድ ሎደር ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ባስቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ከሀገር ውስጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ/2018 ዓ.ም/ ግብር / የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝርየተመዘገቡ:የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፡ታከስ ከሊራንስ እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፣
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤትና ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ከፍል ዋናው መስሪያ ቤት ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መግዛት ይችላሉ፣
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንከ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች ከቴክኒካል አፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል አፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት እስከ ሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት በ5፡00 ይዘጋል።
5. ጨረታው ሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም የቴከኒካል አፈሩ ብቻ በ5፡30 በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት እያግድም።
6. ቴክኒካል ምዘና ያለፉት ተጫራቾች ብቻ ፋይናንሻል ኦፈራቸው ሀምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በ5፡ 00 ሰአት በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈትአያግድም።
7. አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ 011 554 57 71/0920935336
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ
