የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ፈርኒቸር /የቢሮ እቃ/፣የጥገና እቃዎች በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡-ግ/ፋ/ጨ-1/339/2017
የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የቀረበውን ዝርዝር በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች በቀረበው ሎት ዝርዝር መሰረት።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የውድድሩ አይነት |
ምርመራ |
|
1 |
ሎት 1 |
ፈርኒቸር /የቢሮ እቃ/ |
20,000 |
በድምር |
ለ 1 ጊዜ ግዥ |
|
2 |
ሎት 2 |
የጥገና እቃዎች |
20,000 |
በነጠላ ዋጋ |
ለ6 ወር የሚቆይ ግዥ |
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለሁሉም ሎት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (የስራ ፍቃድ) ያላቸው። የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎቱ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት በሆስፒታሉ ግቢ በመቅረብ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ዋናው በስም በታሸገ ኤንቪሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሁሉም ማስገባት ይኖርባቸዋል። መጫረቻ ሰነድ ላይ ሲሞሉ ለሁሉም ሎት ቫትን ወይም TOT ጨምሮ መሆን ይኖርበታል። ለሁሉም ሎቶች የውለታ ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት ውል ይወስዳሉ።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ከባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ጋር አብሮ በቀረበው የጨረታ መመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ንብረቶችን መረካከቢያ ቦታ ሆስፒታል ግቢ ይሆናል። እንዲሁም ሆሉ የቫት ሰብሳቢ (ቆርጦ የሚያሰቀር መሆኑን ይወቁ)
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች በሚከፈትበት ቀን ቢኖሩም ባይኖሩም ከመከፈት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም። የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም በበዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033 241 50 05/ደውለው ይጠይቁን
የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል
