Tender Detail

Tender Details

  • Company Felege Hiwot Comprehensive Specialized Hospital (የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
  • Address ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 13፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0583205738
  • Websitehttps://felegehiwothospital.com
  • Deadline19 Oct 2024, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Materials

የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የዕዳት እቃዎች፣ የህከምና መሣሪያዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የህትመት ሥራዎችና ፍራሽ ማንኛውም ግብርና ታክስ ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶችን ይጋብዛል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር፦ ፈ/ህ/አጠ/ስፔ/ሆ10/2017

 

የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የዕዳት እቃዎች፣ የህከምና መሣሪያዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የህትመት ሥራዎችና ፍራሽ ማንኛውም ግብርና ታክስ ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶችን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የግብር ከፋይነት መለያ /TIN CARD/ ሰርተፊኬት ያላቸው፤

3. አጠቃላይ የአንድ ዓመቱ ድምር የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡

6. በጨረታው አሸናፊዎች የሚለዩት የፅዳት እቃዎችንና ፈርኒቸሮችን በሎት ወይም በአጠቃላይ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት አሸናፊ ሲሆን ስፖንጅ ፍራሽ፣ የህከምና መሣሪያዎችና የህትመት ሥራዎች ግን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሆስፒታሉ ዋና ገ/ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ማንኛውንም ግብር እና ታከስ ጨምሮ ብር 2% /ሁለት ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱ ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡15 ሰዓት ይታሸጋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥዎች ቢሮ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058-3-20-57-38/ 058-2-22-09-16 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፦ ፈስገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባህር ዳር

ፓ.ሳ.ቁ ፡- 47 

ስልክ ቁጥር :-058-2-26-44-12/058-2-22-02-31/058-2-22-09-16

ፋክስ ቁጥር፡- 058-2-26-44-12

ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender