በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2017 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እታዎችን ማለትም ሎት-1 : የተለያዩ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ እቃዎች ፣ ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት-3 የጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መሳርያዎች ፣ ሎት-4 የደንብ ልብስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት : ሎት-5 የህትመት ውጤቶችን ሎት-6 የቋሚ እቃዎችና የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ሎት-7 ለህንፃ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች አድሳትና ጥግና ሎት-8 ለሚኒስትሪሚንግ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ማለትም - ኩኪስ፣ ቆሎ፡ ውሃ፡ ለስላሳ መጠጦች እና የተለያዩ ግብአቶችን ጨምሮ ሎት 9 የላዳ እና የፒክ አፕ የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 10-ለፕላንት፣ ማሽነሪ እና ለመሳርያ እድሳት እና ጥገና ጨረታ ሲሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2017
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2017 በጀት አመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እታዎችን ማለትም ሎት-1 : የተለያዩ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ እቃዎች ፣ ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት-3 የጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መሳርያዎች ፣ ሎት-4 የደንብ ልብስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት : ሎት-5 የህትመት ውጤቶችን ሎት-6 የቋሚ እቃዎችና የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ሎት-7 ለህንፃ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች አድሳትና ጥገና ሎት-8 ለሚኒስትሪሚንግ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ማለትም - ኩኪስ፣ ቆሎ፡ ውሃ፡ ለስላሳ መጠጦች እና የተለያዩ ግብአቶችን ጨምሮ ሎት 9 የላዳ እና የፒክ አፕ የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 10-ለፕላንት፣ ማሽነሪ እና ለመሳርያ እድሳት እና ጥገና ጨረታ ሲሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በየዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TinNo) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት እቃ ለሎት1-50,000/ ሃምሳ ሺ ብር ብቻ / ለሎት 2- 9,000 /ዘጠኝ ሺ ብር ብቻ/ ለሎት 3- 9,000 / ዘጠኝ ሺ ብር ብቻ /ለሎት 4- 9,000/ ዘጠኝ ሺ ብር ብቻ / ሎት 5 -5,900 /አምስት ሺ ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ | ለሎች 6 – 31,558/ሰላሳ አንድ ሺ አምስት መቶ ሃምሳ ስምንት ብር ብቻ/ ሎት 7- 9000/ዘጠኝ ሺ ብር ብቻ/ ሎት 8- 1,000 /አንድ ሺ ብር ብቻ/ ሎት 9-1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ሎት 10-3800 /ሶስት ሺ ስምንት መቶ ብር ብቻ/ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል፡፡ ሲፒኦ ስታስይዙ በሎት ከፋፍላችሁ ከሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ጥቃቅን እና አነስተኛን በተመለከተ በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ከወረዳው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት እንደሚኖረው፣ ለጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝነት የተቋቋሙበትን ህጋዊ ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነጻ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነው እሴትን ለሚጨመሩ / አምራች ለሆኑ/ ሥራ ዘርፎች ብቻ መሆኑንን እናሳውቃለን፡፡ ይሄንን ማስረጃ ካደራጀው አካል በደብዳቤ ተጽፎ ለማያቀርብ ተጫራች የጨረታ ሰነድ በነፃ እንደማይሰጠው እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው ንብረት ከፍል ውስጥ ያስረክባል፡፡
- ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሎት የማይመለስ ብር 150 ( አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 ፈት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ ዋጋ መሙላት አለበት፡ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ እለበት። የጨረታ ሰነዱን አርጅናል እና ኮፒ በሁለት ፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለበት። ይህንን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ተጫራቾች ከውድድሩ ወጪ ይሆናሉ።
- ይህ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን 10:00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋውም በ10ኛዉ ቀን 11፡00 ይሆናል፡፡ ጨረታው በግልጽ የሚከፈተው በ11ኛው (በአስራ አንደኛው) ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግልፅ ይከፈታል።
- የጥገና ስራዎችን በተመለከተ ማለትም የሮቶ ማስቀመጫ፣ ፕላሴንታ አጥር፣ የንብረት ክፍል ቢሮ፣ ላውንደሪ ማስፋፊያ፣ ባዮሜዲካል ቢሮ፣ የአጥር ስራ፣ የግዢ ከፍል ማስፋፊያ፣ የሰው ሃይል ቢሮ ማስፋፊያ እና የኢመርጀንሲ ክፍል ማስፋፊያ የጥገና ስራዎች በተመለከተ የሚወዳደሩት በጠቅላላ ድምር በአነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል። ሌሎች የጥገና ስራዎች ለየብቻ የሚወዳደሩ መሆኑንን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ናሙናውን በመስሪያ ቤቱ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የግዥ ቢሮ 407 ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል፡፡ ቋሚ እቃዎችን በተመለከተ ለማቅረብ ቀላል የሆኑትን በማቅረብ ወይም ደረጃቸውን የሚገልጽ እስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ከውል በፊት 20% ጨምሮ ወይም 20% ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111547348/0111 54 60 29/ 0111 26 80 48 /47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- ጉለሌ ክ/ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ህንጻ ፊት ለፊት
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ
