ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
-
- የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች /እስክርቢቶ ሰማያዊ፣ ጥቁር፣ ፕሪንተር፣ ቶነር ወዘተ ዝርዝሩንና ብዛቱን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጠቀሷል፡፡
- የፅዳት እቃዎች/ የልብስ ሳሙና፣ የገላ ሳሙና፣ ፈሳሽ ሳሙና፣ ሶፍት፣ በረኪና፣ ዲቶል ወዘተ ዝርዝሩንና ብዛቱን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት መመዝገቢያ ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው የብር መጠን በባንክ በተመሰከረበት (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የእያንዳንዱ ዕቃዎች ብራንዳቸውንና ሌሎች የዕቃው መገለጫዎች በጨረታ ሰነዱ መሰረት መገለጽ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው መሰረት ተጫራቹ አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች አሸናፊ መሆኑን ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በሶስት የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በራሱ መጓጓዣ ስቴድየም ወደ ሚገኘው ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ የይሓ ሪል እስቴት ንብረት ከፍል /11ኛ ፎቅ ድረስ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ለአሸናፊው ድርጅት/ ግለሰብ የዕቃዎቹን ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ካስረከበ በኋላ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከድርጅቱ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 8 /ስምንተኛው የሥራ ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 8 /ስምንተኛው የሥራ ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተ ዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት "ይሓ ሲቲ ሴንተር" ህንጻ 2ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር የቢሮ ፡- 011-5-58-01-29/12/03
ሞባይል፡- 09-22-07-95-75/09-11-41-79-04
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
