የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በመርባት ላይ ላሉ ዶሮዎች የሚውል መኖ ጥራቱን የጠበቀ አንደኛ ደረጃ ወቅታዊ በቆሎ ምርት በጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በመርባት ላይ ላሉ ዶሮዎች የሚውል መኖ ጥራቱን የጠበቀ አንደኛ ደረጃ ወቅታዊ በቆሎ ምርት በጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ነጋዴዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና ማዕከሉ በሚፈልገው መጠንና ጥራት ማቅረብ የሚችል፣
- አግባብነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና ካሁን ቀደም በተመሳሳይ ሥራ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒና ኦርጅናል ይዞ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተሞላ ሰነድ ለየብቻ 1 ኦርጅናል፣ 2 ሁለት ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር /CPO/ የተያያዘበት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከፋ ዞን ገቢዎች ባለሥልጣን መ/ቤት በኩል የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር /ብቻ በመከፈል ከቦንጋ ዶሮ እርባታ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 21ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ 22ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል ይከፈታል።
- የጨረታ መዝጊያና መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
- የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም፡።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ማንኛውም ኦርጅናል መረጃ ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።
- የጨረታው አሸናፊ በ7 ቀናት ውስጥ ውል ገብቶ ምርቶችን ማቅረብ ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ፡- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 33/ 0841/ 09 51 41 40 16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የቦንጋ ዶሮ እርባታ ማዕከል
