የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪዎችና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የፅህፈት መሳሪዎችና የፅዳት ዕቃዎች ግዢ ጨረታ
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፅህፈት መሳሪዎችና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ሀ. ሎት -1 የፅህፈት መሳሪዎች
ለ. ሎት -2 ፅዳት ዕቃዎች
በመሆኑም በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ወይም የ2016 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያደሱ ፣ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና ፣ የግብር መለያ ስርትፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- አንዱ ተጫራች በሌላዉ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታዉ የሚያሳግድ ይሆናል::
- ተጫራቶች ከጨረታዉ በኃላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለሚጫረትበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ጨረታዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስት (15) በተከታታይ ባሉት ቀናት ዉስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳሊተምህረት ቤ/ክያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘዉ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታዉን ዝርዝር መረጃ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ በብር 300.00 ብር (ሶስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ::
- ተጫራቾች የጨረታዉ አሽናፊ ባቀረባዉ ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘዉ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም::
- ጨረታ ሰነዶችና ከጨረታዉ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ዋናዉና ኮፒ ፡ ፋይናንሻል ዋናዉና ኮፒ ዶክመንት በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያዉ ሰዓት በፊት ለዚህ በተዘጋጃዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለበት::
- ጨረታው ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘዉ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የማህበሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ ዉስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል::
- አሸናፊዉ ተጫራቾች የጨረታዉ አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ዉጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሳሪዎች እና ፅዳት ዕቃዎችን ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ወይም በዉሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራቶች ያሸነፉትን የፅህፈት መሳሪዎች እና የፅዳት ዕቃዎች በድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣትና ማስረከብ ይኖርባቸዋል::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
- በዚህ ጨረታ የማህበሩ የፋሲሊቲ አስተዳደር መመሪያ እና ፖሊሲ ተግባራዊ ያደረጋል::
ተጫራቾች ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰዉ አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር
አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
ስልክ ቁጥር፡-011-515-06-08
ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 41076
