በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው መግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 01/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው መግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም
- አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች - ሎት 1
- የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች ሎት 2
- የፅዳት እቃዎች እና የደንብ ልብስ - ሎት 3
- የተሽከርካሪ እቃዎች - ሎት 4
- የተለያዩ የቢሮ መገልገያዎች - ሎት 5
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፤
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 703 መግዛት ይችላሉ፤
- የሚያቀርቡት እቃ ዋጋ ከብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወቀረት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በጨረታ ላይ ያወጣናቸው እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት ዕቃ ልዩ ሳምፕል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤት ድረስ ማምጣት አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫት በመጨመር በሰም የታሸጉ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሎት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግዥ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 7ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 703 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ወይም በሚያቀርቡት እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ውል የተገባባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ከቢሮው የግዥ አገልግሎት ዳይሬከቶሬት የውል ስምምነት መፈጻም ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
አድራሻ፡- ሃያ ሁለት መገናኛ ለም ሆቴል ፊት ከፊት ኤም.ኤ ሕንፃ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 01115 57 05 95 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
