Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
  • Address ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 4734508
  • Website
  • Deadline07 Nov 2024, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቶችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ 2017 በጀት ዓመት ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቶችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1 - የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ፣

ሎት 2 - የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣

ሎት 3 - የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ፣

ሎት 4 - የተለያዩ ፈርኒቸሮች

ሎት 5 - የተለያዩ የህትመት ስራዎችን፣

ሎት 6 - የተሽከርካሪ 5,000 እና 10,000 . የመኪና ሰርቪስ፣

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  • በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
  • የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
  • የግብር ከፋይ መለያ ምስከር ወረቀት /TIN Number/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
  • የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል የምትችል መሆን ይኖርባቸዋል፤

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት መግዥያ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ቀርበው በመከፈል ዘወትር በመንግስት ሥራ ሰዓት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /የባንክ ዋስትና/ ለእያንዳንዱ ሎት፡-
  • ለሎት 1 - የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ፤
  • ለሎት 2 - የተለያዩ ኤሌከትሮኒክስ 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ፤
  • ለሎት 3 - የተለያዩ ፈርኒቸሮች 100,000 /መቶ ሺህ ብር/ ብቻ፤
  • ለሎት 4 - የተለያዩ የህትመት ውጤቶች 350,000 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ፤
  • ለሎት 5 - የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ፤
  • ለሎት 6 - የተሽከርካሪ 5,000 እና 10,000 . የመኪና ሰርቪስ  50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት እያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አስራ አምስት/ የመንግስት የሥራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ 1 /አንድ/ ኦሪጂናል እና 1 /አንድ/ ኮፒ ፖስታዎች ለየብቻቸው በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻ ፣ ማዕተምና ፊርማቸውን መሙላት ይኖርባቸዋል።

የጨረታው ሳጥን 16ኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

አሸናፊው ድርጅት በተወዳደረበት ቦታ ንብረቱን የማቅረብ ግዴታ አለበት።

ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል /ቤቱ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጨረታውን ሂደት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት ሂደቱን እያስተጓግልም።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- +251-4-73-45-08-79

በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Save Tender