Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
  • Address ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115579684
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline08 Nov 2024, 4:30 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ ጥቅል -1፤ በ የተለያዩ የፋብሪካ የላብራቶሪ ኬሚካሎች ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ብሔራዊ  ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር : 008/አግ/ኦኩስሩቁ-2/2017

  1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ ጥቅል -1 የተለያዩ የፋብሪካ የላብራቶሪ ኬሚካሎች ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ 90 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፡ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር /supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛው ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ትከከለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-10:30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት 200-600) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ፡-
    1. ካዛንቺስ ከመነኸሪያ ሆቴል በዮናስ ጨርጨር ስጋ ቤት በኩል ወደ አቧሬ በሚወስደው ቀጭን አስፓልት 100 ሜትር ዝቅ ብሎ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮዎች ግቢ ውስጥ ነው::

ስልክ ቁጥር :- +251-11-55-79-684/09-17-82-65-84 ወይም 09-38-30-91-60

አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጥቅል ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) በብር ጥቅል 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሠከረለት 90 ቀን ሲፒኦ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /BID BOND/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀመው አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ መጋዘን ነው::
  3. ጨረታው ሀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 60 ቀናት ነው::
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ 28 ቀናት ነው::
  5. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

ኦሞ-ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ                               አዲስ አበባ ገዥ ማስተባበሪያ ቢሮ

Tel-09-40-20-94-64/09 45 00 21 06               Tel: 09 17 82 65 84/-09-38-30-91-60

       ሀይል ውሃ                                                                 አዲስ አበባ

 

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ

ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ

Save Tender