Tender Detail

Tender Details

  • Company በወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0916856313
  • Website
  • Deadline10 Nov 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት 2017 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት-1 የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ሎት 2- ዘጋቢ ፊልም፣ ሎት-3 ሞተር ሳይክል ግዥ ሲሆኑ፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና 2017 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከዚህ በፊት ላከናወኗቸው ተመሳሳይ ሥራዎች/ አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሶዶ ከተማ ፋይናንስ /ቤት መደበኛ አካውንት ቁጥር 1000018212335 ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
  4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨሪታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
  5. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 430 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 20.000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በታወቀ ባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት ግቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
  8. ዘጋቢ ፊልም የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ሁለንተናዊ ለውጥና ዕድገት ማሳየት የሚችል መሆን አለበት።
  9. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:

     ለበለጠ መረጃ 0916856313 /0916349825/ 0910792939 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender