የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት 1- የግንባታ ዕቃዎች፣ 2- ተሽከርካሪ ጎማ፣ 3- የናይትሮጂን መያዣ /ጃር/፣ 4- የተሻሻለ የንብ ቀፎ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት 1- የግንባታ ዕቃዎች፣ 2- ተሽከርካሪ ጎማ፣ 3- የናይትሮጂን መያዣ /ጃር/፣ 4- የተሻሻለ የንብ ቀፎ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በአቅራቢነት በድረ-ገጽ (EGP) የተመዘገቡ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የመጫረቻ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 15 ባሉት ቀናት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 3:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ በ16ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ያለተጨማሪ ወጪ እስከ ቢሯችን በማምጣት የማስረከብ ሃላፊነት አለበት፡፡
- የጨረታ መክፈቻ በበዓላት ወይም በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር- 046-8-81-33-38/ 046-8-81-02-75 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
አርባ ምንጭ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
