Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
  • Address መገናኛ ከ22 ታክሲ መያዣ ዝቅ ብሎ አማረ አብርሃምና ቤተሰቦቹ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 668 42 07
  • Website
  • Deadline10 Nov 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ከፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 001/2017 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል::


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ከፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 001/2017 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል::

ሎት 1 - አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ፣

ሎት 2 – የጽዳት ዕቃዎች ግዥ፣

ሎት 3 - የህትመት ውጤቶች ግዥ፣

ሎት 4 - የሠራተኞች መታወቂያ፣ የደረት ባጅ ከነማንጠልጠያው፣ ባነር እና ክላሰር ባለ አርማ /ባለ አክሮን/ ግዥ

ሎት 5 - የሥራና ደንብ ልብስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ፣

ሎት 6 - ልዩ ልዩ የአይን መነጽር ግዥ፣

ሎት 7 - የህፃናት ብርድ ልብስ አንሶላ እና የመጫወቻ እቃዎች ግዥ፣

ሎት 8 - የአይቲ እና የኤሌከትሪከ እቃዎች ግዥ፣

ሎት 9 - የህንፃ መሳሪያዎች እቃዎች ግዥ፣

ሎት 10 - የመኪና ጎማዎች፣ ቸርኬና ባትሪ እና የጀነሬተርና ባትሪ ግዥ፣

ሎት 11- የጀነሬተር ግዥ እና ኢንስታሌሽን ሥራ፣ ለኢንስታሌሽኑ የሚያስፈልጉ እቃዎችን ጨምሮ ከነእጅ ዋጋው ግዥ፣

ሎት 12 - የቋሚ እቃዎች ግዥ፣

ሎት 13 - የታሸገ ውሃ ግዥ፣

ሎት 14 - የገብስ ቆሎ (የኦቾሎኒ እና ሽንብራ ድብልቅ)

ሎት 15 - የምንጣፍ እና የመጋረጃ (ከነእጅ ዋጋው ግዥ)

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝርና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም 2017 . በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ /ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ፣
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በጨረታ ሰነዱ ላይ በየሎቶቹ ለጨረታ ማስከበሪያ የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በመመልከት በምትወዳደሩበት ሎት የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ h /CPO/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ከፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነድ ቴክኒካል መግለጫ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባችሁ፤
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች ዓይነት ለመለየት የሚያስችል የእቃዎች ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ ቢቀርብ ይመረጣል፣
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፤
  6. በሎት 10 11 እና 12 ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በሁለት በተለያየ ኢንቨሎፕ ሲሆን በአንደኛው ኢንቨሎፕ ቴክኒካል መግለጫ ኦርጅናልና ኮፒው እና በሁለተኛው ኢንቨሎፕ ፋይናንሺያል ኦርጅናልና ኮፒው እንዲቀርብ እና በቀሪው 11 ሎቶች በዝርዝር ተሞልቶ በአንድ ኤንቨሎፕ ፋይናንሺያልና ቴክኒካል መግለጫ ዋናውንና ኮፒውን ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ማስገባት አለባቸው::
  7. የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣ 11ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 7 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 703 ይከፈታል፣
  8. የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን 5 ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 መውሰድ ይችላሉ፣
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች //ቤቱ መጋዘን ወይም ስቶር ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፣
  11. ቅርንጫፍ /ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

አድራሻ:

መገናኛ 22 ታከሲ መያዣ ዝቅ ብሎ አማረ አብርሃምና ቤተሰቦቹ ህንፃ 5 ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502 ነው::

  • ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ የስልክ ቁጥር፡- 011 668 41 08 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላቹ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክ/ከተማ

አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender