በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተለገጸውን ለፈሳሽ ናይትኖጅን ማሽን የሚያገለግል የሒሊየም ጋዝ እና ለአባላዘር ምርት ለማምረት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን /የአባላዘር ኬሚካሎች/ ህጋዊ ከሆኑ ጋዝ እና ለአባላዘር ምርት ለማምረት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን /የአባላዘር ኬሚካሎች/ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተለገጸውን ለፈሳሽ ናይትኖጅን ማሽን የሚያገለግል የሒሊየም ጋዝ እና ለአባላዘር ምርት ለማምረት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን /የአባላዘር ኬሚካሎች/ ህጋዊ ከሆኑ ጋዝ እና ለአባላዘር ምርት ለማምረት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን /የአባላዘር ኬሚካሎች/ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ቁጥር እሀልማኤ 124/2017 ሎት 1 የሂሊየም ጋዝ እና ሎት 2 ለአባላዘር ምርት ለማምረት የሚያገለግሉ ግብአቶች የአባለዘር ኬሚካሎች ግዥ
|
ሎት ቁጥር |
የእቃው ዝርዝር |
|
ሎት 1 |
የሂሊየም ጋዝ |
|
ሎት 2 |
ለአባለዘር ምርት ለማምረት የሚያገለግሉ ግብአቶች/የአባለዘር ኬሚካሎች |
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚገዙ ግብአቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የአብክመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 69 የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በሎት /ለሂሊየም ጋዝ/ 4000.00 4000.00 እና ለሎት2 የአባላዘር ኬሚካል 6500.00 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲፒኦ /ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ፐርፎርማንስ ቦንድ ወይም ሲፒኦ ባህዳር ከተማ ከሚገኝ ማንኛውም ባንክ መሆን ይኖርበታል፡፡
5. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ዋና እና ቅጅ እና የዋጋ ማቅረቢያ/ፋይናሻል ፕሮፖዛል/ዋና እና ቅጅ እያንዳንዱን ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
6. ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ መታሸግ ያለባቸው ከላይ በተ.ቁ 1 የተጠቀሱትንና ሌሎች አስፈላጊ የቴክኒክ ዶክመንቶች መሆን ይኖርበታል፡፡ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ መታሸገ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ ነው፡፡
7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 4516/058 220 6479 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በ120 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ማቅረብ አለበት፡፡
9. ተጫራቾች በአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጨረታ ሣጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ነገር ግን የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተዘግቶ ይከፈታል፡፡ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት
ባህር ዳር
