Tender Detail

Tender Details

  • Company በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ
  • Address አዳሚ ቱሉ እና አዲስ አበባ አዳሚ ቱሉ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 662 4656
  • Website
  • Deadline03 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች ከሎት 1-5 የተገለጹ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር APPF/04/17

  1. በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች ከሎት 1-5 የተገለጹ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
    1. ሎት 1 ለሰራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አልባሳት እና ጫማዎችን
    2. ሎት 2 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የተለያዩ የፅዳት እቃዎች
    3. ሎት 3 የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ጎማዎች
    4. ሎት 4 የተለያዩ የሰራተኞች የሥራ የአደጋ ደህንነት መከላከያ ዕቃዎች (personal protective safety equipment) ብዛት የተለያየ እና
    1.     ሎት 5 የተለያዩ IT እቃዎች ግዥ መግዛት ይፈልጋል።
  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበት የምስከር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉሙሩክ ሚኒስቴር በጨረታ እንዲሳተፉ የተጻፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኤምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስምና አድራሻ በትክከል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡ ተጫራቶች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦሪጅናሉን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንከ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው የቴኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እስከ ህዳር 24 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 በፊት የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ መከፈቻው እለት ህዳር 24 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል፡፡
  8. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- /ቱሉ 0464419164 (ማዞሪያ) 0991625748 (ግዥ ቡድን) 0991589980 (ንግድ መምሪያ) .. 247 (/ቱሉ) አ.አ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር 011 662 4656 .. 1206 (አ.አ)

 

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ

ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ

Save Tender