በኢቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ የገንዘብ መያዣ ካዝና አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት የጨ/ቁጥር 02/2017ዓ.ም
በኢቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት በ2017 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ የገንዘብ መያዣ ካዝና አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ት/ቤቱ ያሳውቃል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች አግባብነት ያለው ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምስከር ወረቀት ከኢትዮጵያ ገቢዎች ባለስልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በዕቃ አቅራቢዎችና የቫት ተመዝጋቢ ሆነው በ2017 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዢ ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በዘርፉ ለመስራታቸው የሚገልፅ ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱበትን በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በመስሪያ ቤታችን የቃሊቲ የመጀ ደ/ት/ቤት ስም በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጋዜጣ ከወጣበት 11 (አስራ አንደኛው) ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
♦ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 ማስያዣ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% ማሲያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ ከነቫቱ አስገብተው በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በተለያየ በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ለመጨረሻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11 (አስራ አንደኛው) ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ወይም በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት የክፍያ ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቀ.3 ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የለበትም፡፡
- ተጫራቾች ለተጫረቱበት ዕቃ ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት የለውም፡፡
- ለአንድ እቃ ዓይነት መቅረብ የሚችለው ናሙና አንድ ዓይነት ብቻ ሲሆን ሁለት እና ከዚያ በላይ የሚቀርብ ናሙና ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው ዋጋ በተጠየቀው መለኪያ መሆን አለበት ከተጠየቀው ስፔሲፊኬሽን ውጪ በግል ማስተካካል ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
ማሳሰቢያ፡
ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 7 የቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት ቼራሊያ ፋብሪካ ጀርባ 100 ሜ. ገባ ብሎ ይገኛል፡፡ ስልክ ቁጥር፡-0114-439-04-47/0114-71-72-57/0114-39-56-74/0114-62-64-94
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ የመጀ/ደ/ት/ቤት
