በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ/የጽ/መሳሪያ 20.000 ብር 2ኛ/ የፕሪንተር ቀለም 10.000 ብር 3ኛ/የጽዳት ዕቃዎች 800 ብር 4ኛ/የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎች 1000 ብር 5ኛ/ የእንሰሳት መድሃኒት 10.000 ብር 6ኛ/ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች 10.000 ብር 7ኛ/ ደረቅ ጭነት 2000 ብር 8ኛ/ የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያሎች 6000 ብር 9ኛ/የደንብ ልብስ የተዘጋጁ 8000 ብር 10/ደንብ ልብስ ጫማዎች 10.000 ብር 11ኛ ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ 6000 ብር 12ኛ/ፈርኒቸር 3000 ብር 13ኛ/የደን ዛፍ ዘር 2000 ብር 14ኛ/ህትመት 1000 ብር 15ኛ/ የመኪና እቃ መለዋወጫ 3000 ብር 16/የመኪና ጎማና ከለማዳሪ 2000 ብር በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200.000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልተው ኮፒና ኦርጅናል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተዘረዘረው ሎት የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚስጥ ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ወይም በገቢ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቹ በዋጋ መሙሊያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጫረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ድረስ በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጫረታ በተዘጋጀ ሳጥኑ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ዕቃውን በሚ/ወ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች ባለት ንብረት ክፍል ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ውድድሩ እንደአስፈላጊነቱ በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊሆን ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች በአካል ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ላይ የጨረታ ሰነድ የመጨረሻ ማስገቢያ ከጠዋቱ 3:30 ሆኖ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የደንብ ልብስ የተዘጋጁ፣ የደንብ ልብስ ጫማዎች እና የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙና ሳምፕል ተጫራቹ ያቀርባል የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያሎች ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ናሙና ሳምፕል/ መ/ቤቱ ያቀርባል ተጫራቾች በተጨማሪ ለፕሪንተር ቀለም ከአምራቹ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስ/ቁ 0111170171 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
