የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት ዓመት የእቃና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት ዓመት የእቃና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
ሎት 1. የሬዲዮ አፋን ኦሮሞ ተከታታይ ድራማ በድጋሚ የወጣ፣
ሎት 2. የሙቀት መቆጣጠሪያ /Air Conditioner/ ግዥ በድጋሚ የወጣ፣
ሎት 3. ዲጂታል መታወቂያና ባጅ ማተሚያ ማሽን ግዥ በድጋሚ የወጣ፣
ሎት 4. የጽዳት ዕቃዎች ግዥ፣
ሎት 5. የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ፣
ሎት 6. የደንብ ልብስ ግዥ፣
ሎት 7. የተሽከርካሪ ጎማ እና ጌጣጌጥ ግዥ፣
በጨረታ ቁጥር አ.ሚ.ኔ.ብ.ግ.ጨ.005/2017 በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00፣ ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00፣ ለሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00፣ ለሎት 4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00፣ ለሎት 5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00፣ ለሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00፣ ለሎት 7.የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ጨረታዎች ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ ቢሮ ቁጥር 28 የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 34 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ የመክፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን / ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፤ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 011 1 11 63 82 መደወል ይችላሉ፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
