Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
  • Address በካፋ ዞን ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0917916439
  • Website
  • Deadline27 Nov 2024, 3:30 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Materials

የደ/ም/ኢ/ህ/ክ / መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ማለትም፤ በሎት 1 ህንጻ መሳሪያ /ኮንስትራከሽን/፣ በሎት 2 ጀኔራል ሜታል ፋብርኬሽን ፣ በሎት 3 ፕላምፕንግ /የቧንቧ/ እቃዎች ፣ በሎት 4 ፈርኒቸር ሜኪንግ እቃዎችን/ ፣ በሎት 5 የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች፣ በሎት 6 አይሲቲ ዕቃዎች፣ በሎት 7 አግሮፕሮሰሲንግ ፧ በሎት 8 ሆቴልና ቱሪዝም፣ በሎት 9 የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ በሎት 10 ኤሌክትሮ ቴክኖሎጂ ፣በሎት 11 አውቶሞቲቪ እቃዎች፣ በሎት 12 የጋርመንት እቃዎች እና በሎት 13 ሰርቬይንግ እቃዎችን በሙያ መስክ ከተሰማሩ ከህጋዊ ነጋዴዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ማስታወቂያ  ጥር  BPTC01/2017

የደ//// / መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2017 በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ማለትም፤ በሎት 1 ህንጻ መሳሪያ /ኮንስትራከሽን/ በሎት 2 ጀኔራል ሜታል ፋብርኬሽን በሎት 3 ፕላምፕንግ /የቧንቧ/ እቃዎች በሎት 4 ፈርኒቸር ንግ እቃዎችን/ በሎት 5 የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች፣ በሎት 6 አይሲቲ ዕቃዎች፣ በሎት 7 አግሮፕሮሰሲንግ በሎት 8 ሆቴልና ቱሪዝም፣ በሎት 9 የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ በሎት 10 ኤሌትሮ ቴክኖሎጂ ፣በሎት 11 አውቶሞቲቪ እቃዎች፣ በሎት 12 የጋርመንት እቃዎች እና በሎት 13 ሰርቬይንግ እቃዎችን በሙያ መስ ከተሰማሩ ከህጋዊ ነጋዴዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተወዳዳሪዎች -

  1. በሙያ መስክ ወይም በዘርፉ የተመዘገቡና ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ህጋዊ ዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ስለመሆናቸው እና የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /specification/ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 2 ቀን ጀምሮ 13 ተከታታይ ቀናት አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ተግባረእድ ፖሊ /ኮሌጅ ግቢ እና ቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ/ንብ/ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ በኮሌጁ የሂሳብ ቁጥር 1000029122877 ላይ የማይመለስ 200 ብር በማስገባት የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች በመለየት በአይነታቸው እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ዋናና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዘርፍ የተጫራቾችን ስም ወይም ድርጅት በመፃፍና ማህተም በመምታት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 2 ቀን ጀምሮ 13/አስራ ሶስት/ ተከታታይ ቀናት ወይም ጨረታ የሚታሸግበት ቀንና ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሁለቱንም በእናት ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ብቻ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ቢድ ቦንድ እና የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  5. አሸናፊዎች ባሸነፉበት የዕቃ ዋጋ መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን እስከ ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ የትራንስፖርትና ማንኛውም ወጪ በመቻል በውሉ ላይ በሚጠቀሰው ቀን ማቅረብና ማስረከብ አለባቸው። ለማያቀርቡ ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡
  7. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 15ኛው ቀን ከቀኑ 930 እስከ 1000 ሰዓት ይሆናል፡፡
  8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት እለት ጀምሮ 60 ቀናት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ግዥ ንብ /አስ/ ቢሮ ቁጥር 01 ጋዜጣው ከወጣበት ልክ 18ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በጨረታ ፈቻ ወቅት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አይከለከልም፡፡ እለቱ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደ የሚቀጥለው ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይተላለፋል፡፡
  10. በጨረታ ሰነዱ ላይ ማንኛውንም ማስተካከያ ማድረግም ሆነ ከቀረበው ሰነድ ዉጭ መሙላት አይፈቀድም፡፡
  11. ተጫራቾች ባሸነፉበት እቃ የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ ከአታችሜንት ጋር አያይዘው ማቅረብ ወይም የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ የማይጠቀሙ ከሆነ የማይጠቀሙበት ምክንያት ከገቢዎች /ቤት ደብዳቤ በማስደገፍ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ መረጃ - በስልክ ቁጥር 0917916439/0913466023/0917824661/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በደ/ም/ኢ/ህ//መ/ክህ/ቴክ/ ቢሮ  የቦንጋ  ፖሊ  ቴክኒክ  ኮሌጅ

Save Tender