የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት
የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ግዢ በድጋሚ የወጣ
ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ሀ. ሎት-1 የምግብ ቁሳቁስ (ዳይጄስቲቭ ብስኩትና የህፃናት ወተት)
ለ. ሎት-2 ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች (የህጻናት ዳይፐር፣ የወንዶችና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ፉልሴት ማለትም የገላ ሳሙና፣ የልብስ ሳሙና፣ ሶፍት፣ ፎጣ፣ የጥርስ ሳሙና እና ብሩሽ ሆኖ የሴቶቹ ሞዴስ ይጨምራል)
በመሆኑም በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከጨረታ ስነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ የመንግስት ግብር የከፈሉ ወይም የ2016 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያደሱ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና ፣ የግብር መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- አንዱ ተጫራች በሌላዉ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታዉ የሚያሳግድ ይሆናል::
- ተጫራቾች ከጨረታዉ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተመሳሳይ አስራ አምስት (15) በተከታታይ ባሉት ቀናት ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በጉርድ ሾላ ሳሊተምህረት ቤ/ክያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ ከሚገኘዉ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት የጨረታዉን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በብር (600) ብር (ስድስት መቶ ብር) በመግዛት የጨረታ ሰነዳችሁን እስከ ኅዳር 18/ 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጃዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ተጫራች ጨረታውን አሸንፎ ባቀረበዉ ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘዉ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ድርጅቱ ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም::
- ጨረታ ሰነዶችና ከጨረታዉ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ዋናዉና ኮፒ እና ፋይናንሻል ዋናዉና ኮፒ ዶክመንት በፖስታ በማሽግ ከጨረታ መዝጊያዉ ሰዓት በፊት ለዚህ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለበት::
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች የአገልግሎት ጊዚያቸው አንድ አመትና ከዚያ በላይ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም ለሚያቀርቧቸው ቁሳቁሶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ድርጅቱ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የአንዱን እቃ ዋጋ ተመልክቶ በትእዛዙ መጠኑ/ብዛቱ ላይ እስከ 25 በመቶ የመጨመር ሆነ የመቀነስ መብት አለው::
- ጨረታው ኅዳር 18/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 በጉርድ ሾላ በሚገኘዉ ሳሊተ ምህረት ቤ/ክያን ፊት ለፊት ድራር ሞል አጠገብ በሚገኘዉ የማህበሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ ዉስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል::
- አሸናፊዉ ተጫራች የጨረታዉ እሸነናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ምግብነክ እና ምግብነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ከ7ቀን ባልበለጠ ግዜ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በድርጅቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
ተጫራቾች ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት
ስልክ ቁጥር፡ 011-515-06-08
ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ 41076
