አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር ማህበሩ በ2017 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያዎች፤ ሎት 2 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡- AWACH/NCB/G/01/2017/2024
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር ማህበሩ በ2017 በጀት ዓመት
ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያዎች፤
ሎት 2 የፈርኒቸር እቃዎች፣
ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች/ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከገቢዎች ሚኒስቴር በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል አዋሬ፣ ኤድና አዲስ ሆቴል ፊት ለፊት ገባ ብሎ፣ አጋር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንከ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁና የተጠየቀውን መስፈርት የሚያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃና አገልግሎት ግዢዎች በሙሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው በሎት 1 የተገለጹት እቃዎች በተመለከተ ከየአይነቱ አንድ አንድ ናሙና የድርጅታቸውን ማህተም አድርገው፤ የናሙናዎቹን ዝርዝር በሁለት ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት አስቀድሞ ለማህበሩ የግዥ ሰራተኛ አስፈርመው ማስረከብና አንዱን ኮፒ መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-5-57-73-41 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- አዋሬ፣ ኤድና አዲስ ሆቴል ፊት ስሬት ገባ ብሎ፣ ስጋር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፡ ቢሮ ቁጥር 201 አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃሳ/የተ/መሠ/የህብረት ሥራ ማህበር ዋና ቢሮ
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የመሰረታዊ /የኅ/ሥ/ማ
