Tender Detail

Tender Details

  • Company የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ጽ/ቤት
  • Address ባሌ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 02224400023
  • Website
  • Deadline15 Dec 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Food And Beverage

የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ጽ/ቤት በማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውሉ ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ የሚቀርብ የምግብ እህሎች፣ ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::


የጨረታ  ማስታወቂያ

      የጨረታ  ቁጥር  // 04/2017

የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት /ቤት በማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውሉ ከጥር 1 ቀን 2017 / እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 / ድረስ የሚቀርብ የምግብ እህሎች፣ ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::

ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ::

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ 2017 . የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን (Trade license) የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የቲኦቲ (TOT) የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፈኬት ምዝገባ ማስረጃ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (Supplier list) ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመፈል ከባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ከቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) የያዘ ሲፒኦ ብቻ እውቅና ካለው ባንክ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው::
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የቴከኒካል ኦሪጂናል ሰነድ 2017 . የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን (Trade license) የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፊኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (Supplier list) ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች በመግዛት ኦሪጂናል ፋይናንሺያል (ዋጋ የተሞላባት) ሰነድ ፋይናንሺያል ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ ሶስቱንም ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት እለት እና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ::
  6. እያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
  7. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
  9. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው 5 ቀን በኋላ 6ኛው ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ውስጥ /ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው፡፡

ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ ማብራሪያ:- በስልክ ቁጥር 02224400023/0932311224 ደውለው ይጠይቁ

 

የባ ዞን ማረሚያ ቤት /ቤት

Save Tender