Tender Detail

Tender Details

  • Company በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክ/መ/ የአሶሳ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ
  • Address አሶሳ ፡ ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-17-85-62-51
  • Website
  • Deadline20 Dec 2024, 1:30 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Food And Beverage

የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከጥር 01 ቀን 2017 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ያለውን ቀለብና የተለያዩ የወጥ አህሎች እና የንፅህና እቃዎችን ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከተውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከጥር 01 ቀን 2017 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 . ድረስ ያለውን ቀለብና የተለያዩ የወጥ አህሎች እና የንፅህና እቃዎችን ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከተውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሠርገኛ ጤፍ፣ ነጭ ማሽላ፣ ጥራት ያለው በቆሎ፣ ከአተር የተፈጨ ሽሮ፣ ሻይ ቅጠል፣ ኤግል ካሜራ (እርሾ) ክኖር የወጥ ማጣፈጫ፣ ቀይ ሸንኩርት፣ በርበሬ፣ ፓስታ፣ አጃክስ፣ ጨው፣ ባቄላ ክክ፣ ሩዝ የሚቀቀል፣ ድንች፣ የዳቦ ዱቄት ነ፡ ስኳር፣ የምግብ ዘይት ማጂ ማክስ (Magi Max) ዳቦ ማሻሻያ፣ ምስር ክክ፣ አተር ክክ እና እርድ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታ  መወዳደር  የምትፈልጉ  ተጫራቾች፡-

  1. በተሰማሩበት የስራ መስክ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የገንዘብ ሚኒስቴር የክልሉ ///ቢሮ የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ እና የውል ስምምነት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት አሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ //ንብ/አስ/ቢሮ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ማስያዣ/10,000/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በተቋሙ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ወይም በከፊል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት፡፡
  8. አሸናፊ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው 16ኛው ቀን ከቀኑ 730 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 800 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ዕለት ባይገኙም የጨረታ አከፋፈት ሂደቱ አይስተጓጎልም፤ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀናት በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው በሚከፈትበት አብሮ መቅረብ አለበት
  11. ቫት ተመዝጋቢ ወይንም ቲአቲ ደረሰኝ ያሳተሙ መሆን አለባቸው::
  12. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ

ለበለጠ መረጃ ፡- 09-17-85-62-51/09-12-79-31-46

ማሳሰቢያ፡- ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት በገዛችሁት ሰነድ ብቻ ይሆናል።

ሰነዱ አስፈለጊው መረጃ ተሞልቶ የድርጅቱ ማሕተም ተመትቶ ከዋጋ ዝርዝር ጋር የሚመለስ ይሆናል፡፡

 

የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ

Save Tender