Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise (የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት) (ኢኢግልድ)
  • Address በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ አራት መንታ በሚወስደው መንገድ ጣልያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111281529
  • Websitehttp://www.eiide.com.et/web/guest/about-us
  • Deadline20 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ሎት 1 የደንብ ልብስ አቅርቦት እና ሎት 2 የሞባይል ስልክ ቀፎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ)

ሎት 1 የደንብ ልብስ አቅርቦት እና

ሎት 2 የሞባይል ስልክ ቀፎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከድርጅቱ የግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቶች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጂናልና ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ 16ኛው ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና /ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የደንብ ልብስ ናሙና (ሳምፕል) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 100,000 (አንድ መቶ ) እና ለሎት 2 ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ... ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡

በጨረታ መክፈቻ ሰዓት የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉለውም ፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡-  አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ /ቤት)

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ ፡- በስልክ ቁጥር 011-1-57-24-97/ በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

Save Tender