Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service (EPSS) (የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት)
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2765-294
  • Websitehttps://epss.gov.et/
  • Deadline10 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Materials

የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆነ ያገለገሉ ወረቀቶችና የህትመት ውጤቶች፣ ፎም ፓክ፣ ካርቶኖች፣ የእንጨትና ፕላስቲክ ፓሌቶች፣ ጎማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::


የጨረታ ማስታወቂያ

   የጨረታ  ቁጥር  መአኤ/01/2017

 

የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆነ ያገለገሉ ወረቀቶችና የህትመት ውጤቶች፣ ፎም ፓክ፣ ካርቶኖች፣ የእንጨትና ፕላስቲክ ፓሌቶች፣ ጎማዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም  ተጫራቾች  ከዚህ  በታች  የተመለከቱትን  ነጥቦች  በማሟላት  ቀርበው  መወዳደር  ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ውስጥ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፤
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎቹ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ የዕቃዎቹ የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።  የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  5. ጨረታው ታህሳስ 1 ቀን 2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 815 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 4 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን 5 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-2765-294 ወይም 011-2783-008 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  10. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት

Save Tender