Tender Detail

Tender Details

  • Company ሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen Fuer Menschen)
  • Address ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 471 42 91
  • Websitehttps://en.menschenfuermenschen.at/
  • Deadline14 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Construction Materials And Raw Materials

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን ቡሬ የገጠር ከተማ እያስገነባ ላለው የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ እና ግንባታ እቃዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን ቡሬ የገጠር ከተማ እያስገነባ ላለው የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ እና ግንባታ እቃዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም  ከዚህ  በታች  የተገለፁትን  መስፈርቶች  የምታሟሉ  እንድትጫረቱ  ተጋብዛችኋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት 2017 . የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የንግድ ምዝገባና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይ ምዝገባ (TIN Number) እና VAT ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን የጨረታ ሰነድ ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ በመቅረብ በማይመለስ በብር 100 (አንድ መቶ ብር) ገዝተው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፣የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልከ (የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) 2% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፤
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በአንድ ፖስታ ሌሎች የተጠየቁ የንግድ ሰነዶችን በሌላ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው፡፡ ፖስታዎቹም የዋጋ ማቅረቢያ እና የንግድ ሰነዶች በሚል ተፅፎባቸው ይቀርባሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-5 ያሉትን ካላሟሉ ከጨረታ ይሰረዛሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መጠቀም አለባቸው፡፡ ተጫራች የሚያቀርበው የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላስቀመጠው የእቃው አይነት እና / ወይንም መስፈርት (Specification) መሆን አለበት፤
  8. ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የአንዱን እቃ ዋጋ በትከክል መሞላት አለበት፤ አቅርቦቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የማይመለከተው ከሆነ በሚሰጡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታከስ አይካተትም፤
  9. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከሞሉ በኋላ ጠቅላላ ድምር ወደ ጎንም ወደታችም ደምረው ማስቀመጥ አለባቸው፤ የድምር ስህተት ቢኖር የተሰጠው ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል፤
  10. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤
  11. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጥል ለእያንዳንዱ ዕቃ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፤
  12. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ ስርዝ ድልዝ ካለ በአቅራቢው መፈረም አለበት፤
  13. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ቀናት ይቆይና በአስረኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 830 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና /ቤት ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል፤ አስረኛው ቀን ቅዳሜ/ እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል፤
  14. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ በሶስት የስራ ቀናቶች ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ጥራቱ በድርጅቱ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፤ ይህንን ባያደርግ ወይም ቀይሮ ያመጣው ዕቃም ጥራቱ ተቀባይነት ካላገኘ ግን እቃውን ማቅረብ እንዳልቻለ ተቆጥሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ወይም የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስለትም፤
  15. አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህንን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም አይነት ክፍያ መጠየቅ አይችልም፡፡ /ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም፤
  16. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፤
  17. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ Menschen fur Menschen ስም አዘጋጅተው በፖስታ በማሸግ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  18. የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ ወይም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል፤
  19. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
  20. ተጫራቾች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችሉም፤
  21. በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በከፊልም ሆነ በሙሉ ማቅረብ ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ውል ማስከበሪያ ሙሉ በሙሉ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፤
  22. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 0114 71 42 91 / 0114 71 43 58 በሥራ ሰዓት ደውሎ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

ሰዎች  ለሰዎች  ድርጅት

 

Save Tender