የቤ/ጉ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ እና ፕላን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሃገር አቀፍ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ እና ፕላን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሃገር አቀፍ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ለመወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች
ሎት 1. የሠራተኛ ደንብ ልብስ፣ ሎት 2 የተሽከርካሪ ጎማ፣ ሎት 3 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 4 ፈርኒቸሮች፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክሶች፣ ሎት 6 ፕሪንተር ቀለሞች፣ ሎት 7 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 8 ለአይሲቲ ቁሳቁሶችን እና ሎት 9 ሞተር ሳይክል
- በዘርፉ የተሰጠ እና አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የመንግስት የስራ ቀናት ድረስ ብቻ በማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል አዲስ አባበ 6 ኪሎ ፕላን ኮሚሽን በመደበኛ የመንግስት የስራ ሰዓት ብቻ በአካል በመቅረብ የእቃውን ዝርዝር መግለጫ እና የዋጋ መመሪያ ሰነድ በመውሰድ / መወዳደር ይችላሉ።
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸው በትከክል ጽፈው በመፈረምና የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት እለት አንስቶ ባሉት አስራ አምስት የስራ ቀናት ድረስ ብቻ ዋጋውን ሞልተው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በ16ኛው ቀን ረፋድ 04:30 ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ቢድ ቦንድ /bid bond/ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ከኢት ብሄራዊ ባንክ እና እውቅና ካላቸው ባንኮች የተረጋገጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 5,000 /አምስት ሺህ/ በጥሬ ማስያዝ አለበት ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ቢሮው ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ሳይለውጡና ሳይነካኩ በትክክል በዚሁ ሰነድ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ለበለጠ መረጃ:- 0577750674 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቤ/ጉ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ
አሶሳ
