በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስ/ር ኮሚሽን የስልጤ ዞን የወራቤ ማረሚያ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን በሎት ሎት 1 ቀጭቀጭ የወጣለት የተበጠረ ሰርገኛ ጤፍ፣ በቆሎ፣ አተር፣ ፉርኖ ዱቄት፣ ባቄላ በሎት 2 አንበሳ ሻይ ቅጠል፣ ጨው፣ ስኳር፣ ዘይት በሎት 3 ጎመን ዘር፣ የተፈጨ በርበሬ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ሞኮረኒ፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ምስር ክክ ፣ አተር ክክ እና የተለያዩ ቅመማ ቅመም በሎት 4 የማገዶ የባህር ዛፍ እንጨት ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017

በዚህም መሠረት ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመደቡ
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ
- ቫት/VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ይሆናል።
- አሸናፊው ማንኛውንም ወጪ በራሱ ሸፍኖ ዕቃዎችን ወራቤ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታው ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺ ብር) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅና ያለው የፋይናንስ ተቋም የተረጋገጠ ቼክ፤ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፤ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆን ተጫራቾች በአሸነፉባቸው ዕቃ አይነት 10% ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት በዘርፉ የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውንና የመወዳደሪያ ሂሳባቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0911804123 መጠየቅ ይችላሉ።
የወራቤ ማረሚያ ተቋም