Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Athletics federation (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን)
  • Address ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116-47-97-94
  • Websitehttps://eaf.org.et/
  • Deadline03 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Camera

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በተፃፈልን ደብዳቤ መሠረት የፌዴሬሹኑ ህንፃ በሚገኝበት አካባቢ ከወንጀል ለመከላከል ይረዳ ዘንድ የውጪ የደህንነት ካሜራ መግጠም ስለፈለገ በቀረበው Spacification መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከየካ /ከተማ ፖሊስ መምሪያ በተፃፈልን ደብዳቤ መሠረት የፌዴሬሹኑ ህንፃ በሚገኝበት አካባቢ ከወንጀል ለመከላከል ይረዳ ዘንድ የውጪ የደህንነት ካሜራ መግጠም ስለፈለገ በቀረበው Spacification መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ  መሠረት -

  1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደስ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ::
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር የሚያቀርቡትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 430 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል::
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል::
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይኖርባቸዋል::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሣጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ከቢሮ መውሰድ ይኖርባቸዋል::
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ :- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ - 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለጡ መጠየቅ ይችላሉ::

ፋክስ - 0116-45-08-79

.. - 13336

 

የኢትዮጵያ  አትሌቲክስ  ፌዴሬሽን

Save Tender