የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተለያየ ጊዜያት ኤከስፖርት ለሚያደርጋቸው እና ለአገር ውስጥ ግብይት ምርቶች መያዥያነት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸውን የፕላስቲክ ከረጢቶች የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር :- ኢንሥኮ - ማዕከል ግዥ/ብግጨ 08/2017
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተለያየ ጊዜያት ኤከስፖርት ለሚያደርጋቸው እና ለአገር ውስጥ ግብይት ምርቶች መያዥያነት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸውን የፕላስቲክ ከረጢቶች የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ለ 2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታ መክፈቻው ቀን በኋላ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 450.00 (ብር አራት መቶ ሃምሳ ) በመክፈል ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡00 – 10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 -6፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻ በመያዝ ብሎክ 1 ቢሮ ቁጥር 206 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል።)
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው። ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ቴከኒክ እና ፋይናንስ ሰነድ በግልጽ ከፋፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1 (አንድ)
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 50,000.00 (አምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የፕላስቲክ ከረጢት ናሙና መቅረብ አለባቸው።
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም ስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ደብረዘይት መንገድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት
ፖ.ሳ.ቁ 7858
ስልክ ቁጥር 0114 4167345/011 4669336
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
