በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ የመረጃ ቴከኖሎጂ ዕቃዎች እና የሰነድ ማጓጓዣ ጋሪ፣ የመፀዳጃ ቤት ጥገና ዕቃዎች እና የሞተር ሳይክል ጎማ እና የመኪና ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፡- 02/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕቃዎች እና የሰነድ ማጓጓዣ ጋሪ ፣ የመፀዳጃ ቤት ጥገና ዕቃዎች እና የሞተር ሳይክል ጎማ እና የመኪና ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና TIN ሰርተፍኬት ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፤
- ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው፤
- ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ የደንብ ልብስ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር)፤ ለሎት ሁለት አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎች 4,300 (አራት ሺህ ሶስት መቶ ብር)፤ ለሎት ሦስት የህትመት ውጤቶች ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር)፤ ለሎት አራት የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕቃዎች እና የሰነድ ማጓጓዣ ጋሪ 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር)፤ ሎት አምስት የመፀዳጃ ቤት የጥገና ዕቃዎች 500 (አምስት መቶ ብር)፤ ሎት ስድስት የሞተር ሳይክል ጎማ እና የመኪና ዕቃዎች 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በቅሎ ቤት (ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት) ዳቢ ቤኛ ታወር 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መከፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር ፡- 011-4-70-52-41/ 011-4-70-58-17
አድራሻ ፡- በቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ዳቤ ቤኛ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
