በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የህንጻና ከተማ ዘርፍ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከርና ፓምፕ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ.ኢ.ኮ.ሕ.ከ.ዘ.ብ.ግ.ጨ.001/2017
በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የህንጻና ከተማ ዘርፍ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከርና ፓምፕ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ2ኛ ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ ገበያ በሚወስደው መንገድ ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ አጥር ቀጥሎ በሚገኘው አስፋልት መንገድ በግምት 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የህንጻና ከተማ ዘርፍ የዘርፍ ፋይናንስ አገልግሎት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ2ኛ ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 20ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ20ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዘርፉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡-
- ሳሪስ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10
- በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሕንጻና ከተማ ዘርፍ
- የበለጠ መረዳት ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር +251-11-440 36 47 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሕንጻና ከተማ ዘርፍ
