በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ዙር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2017
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ዙር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እያሳወቅን::
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን |
|
1 |
ስቴሽነሪ |
ሎት 1 |
15,000 ብር |
|
2 |
የፅዳት እቃዎች |
ሎት 2 |
15,000 ብር |
|
3 |
ፈርቸር እቃዎች |
ሎት 3 |
10,000 ብር |
|
4 |
የመስተንግዶ አቅርቦት |
ሎት 4 |
8000 ብር |
|
5 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
ሎት 5 |
5,000 |
|
6 |
የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት |
ሎት 6 |
5,000 |
|
7 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
ሎት 7 |
5,000 |
|
8 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች |
ሎት 8 |
20,000 |
- በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘመኑ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ ቲን ነምበር ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት::
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ቢፈጠር ከፊት ለፊቱ ፊርማ ሊኖረው ይገባል አለበለዚያ የተሞላው ዋጋ ተቀባይነት የለውም::
- የጨረታ ሰነዱ አንዱ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች ሊረዱት የሚገባ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተካተቱ ችግሮች ቢያጋጥሙን በግዥ መመሪያው መሰረት የሚዳኝ ይሆናል።
- ጨረታውን ለማወዳደር የእቃ ጥራት የዋጋ ዝቅተኝነት ወ.ዘ.ተ ግምት ውስጥ የምናስገባ ይሆናል::
- ጨረታውን ለማዛባት ወይም እንቅፋት ለመፍጠር የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በህግ እንዲከሰሱ ይደረጋል::
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ እንዲሁም ከስፔስፊኬሽን ወይም ካቀረቡት ናሙና ውጭ ማቅረብ አይችሉም።
- ጨረታው በሁለት ኢንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጂናል እና ኮፒ የጨረታ ሰነድ የሚል ጽሁፍ እንዲሁም ሙሉ የጨረታ ሰነዱ ኮፒ ተደርጎ በአቅራቢው ድርጅት ማህተም ተረጋግጦ ተመላሽ መሆን ይገባል::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል::
- ተጫራቾች መጫረቻ ሰነዶችን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 የሚታሽግ ሲሆን ቀጣዩ ቀን የስራ ቀን ከሆነ ጠዋት 3፡30 ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈትና የሚለይ ይሆናል፡
- የመወዳደሪያ ሰነዱን በቦሌ/ክ/ከ/ወ/13 አስተዳደር እና ፋይናንስ 4ኛ ፎቅ በመቅረብ አንድ ሎት ዋጋ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ውሉን ከተዋዋሉ በኋላ እቃውን በ10 ቀናት ውስጥ በአስተዳደሩ ግቢ ውስጥ ባለው ንብረት ክፍል አጠናቀው ማስገባት ይኖርባቸዋል
- ጽ/ቤቱ 20% መጨመር ወይም 20% መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ -
የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ፡- ገርጂ ታክሲ ተራ ወረዳ 13 አስተዳደርና ፋይናንስ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 41 በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር ፡- 0118931655 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር እና ፋይናንስ ጽ/ቤት
