የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት 1- ቶታል ስቴሽን /Total station/ 2- ሞተር ሳይክል፣ 3- የተለያዩ ማጣቀሻ መጽሐፍት፣ 4- ናይትሮጂን ጃር፣ 5- የልብስ ስፌት ማሽን፣ 6- የልዩ ፍላጎት አጋዥ ግብዓቶች፣ 7- ዊልቸር፣ 8- Walking Tractor /Harvest/፣ 9- የስፖርት ትጥቆችን፣ 10- ካሜራ፣ 11- ፈርኒቸር፣ 12-ሞንታርቦ፣ 13- መበየጃ ማሽን፣ 14- ኤሌክትሮኒክስ፣ 15- የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በአቅራቢነት ድረ-ገጽ (e-GP) የተመዘገቡ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የመጫረቻ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ባሎት ቀናት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1-ቶታል ስቴሽን /Total station/ 2- ካሜራ፣ 3- ሞተር ሳይከል ብር 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ሌሎች ዕቃዎች ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በግዥና/ ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እስከ 3:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣ በ16ኛው ቀን በ3:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
- ማንኝውም ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ያለተጨማሪ ወጪ እስከቢሯችን በማምጣት የማስረከብ ኃላፊነት አለበት፡፡
- የጨረታ መክፈቻው በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-8- 81-33-38/ 046-8-81-02-75 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ