የግል ድርጀት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግል ድርጀት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች ማለትም
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
የጽህፈት መሣሪያዎች፣
ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፤
የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ አገልግሎት፣
የቦቴ ውሃ አቅርቦት አገልግሎት፣
የተሽከርካሪ ጎማዎች፣
የደንብ ልብስ፣
የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጸውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን እና በናሙና መሰረት አሟልቶ ላልቀረበ ማንኛውም ሁኔታዎች ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የተጫራች/ የአቅራቢው/ ድርጅት ይሆናል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና በአስተዳደሩ ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የደንብ ልብስ፣ የጽ/መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ ጎማዎች ናሙና /ሳምፕል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በአስተዳደሩ ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ዕቃዎቹ ሙሉ በሙሉ ኦሪጅናል መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒው ቴከኒክና ፋይናንስ በተናጥል በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልጽ መጻፍ ይኖርበታል። እንዲሁም በአስተዳደሩ ተዘጋጅቶ በጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሞላት አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ላሸነፉባቸው ዕቃዎች ከጠቅላላ ዋጋ 10/100 ለድርጅቱ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታው አሽንፎ በወቅቱ ውል ለማሰር ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ዋስትና ለአስተዳደሩ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት እና የቦቴ ውሃ አቅርቦት ግዥ ለአንድ ዓመት ውል በመያዝ የሚሰራ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- አስተዳደሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን ፡- አዲስ አበባ መገናኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም
የአስተዳደሩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ
ለበለጠ ማበራሪያ ስልክ ቁጥር ፡-251-111-56 88 90/0111 53 03 73 መደወል ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
ግዥው ዓይነት |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን |
ምርመራ |
|
ሎት 1 |
የውሃ ፓምፕ አቅርቦት እና ቴክላ የሚያስፈልገውን ዕቃዎች በማቅረብ 15(አስራ አምስት ፎቅ ላለው ህንፃ) |
እና 0012/2017 |
100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ |
|
|
ሎት 2 |
ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች |
0013/2017 |
50,000.00 /አምሳ ሺህ ብር ብቻ |
|
|
ሎት 3 |
የጽህፈት እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
014/2017 |
30,000.00/ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ |
|
|
ሎት 4 |
ልዩ ልዩ ቢሮ መሳሪያዎች |
015/2017 |
5,000 /አምስት ሽህ ብር ብቻ/ |
|
|
ሎት 5 |
የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድ አገልግሎት |
016/2017 |
5,000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ |
|
|
ሎት 6 |
የደንብ ልብስ ግዥ |
017/2017 |
10,000/አስር ሺህ ብር ብቻ/ |
|
|
ሎት 7 |
የጽዳት ዕቃዎች |
018/2017 |
5,000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ |
|
|
ሎት 8 |
የተሽከርካሪ ጎማዎች |
019/2017 |
30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ |
|
|
ሎት 9 |
ንጽህ የቦቴ ውሃ የሚያቀርብ |
020/2017 |
5,000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ |
|
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
