የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዘይት ባለ 5 ሊትር፣ መኮረኒ፣ ሩዝ፣ ምስር ክክ፣ የተከካ የሽሮ እህል (አተር) እና የተለያዩ አትክልቶችን ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- ADA/08/25
የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዘይት ባለ 5 ሊትር፣ መኮረኒ፣ ሩዝ፣ ምስር ክክ፣ የተከካ የሽሮ እህል (አተር) እና የተለያዩ አትክልቶችን ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት በመገኘት አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር በኢትዮ-ቻይና መንገድ ወንጌላዊት ህንፃ ፊት ለፊት ባለው መንገድ ማሪስቶፕስ ክሊኒክ ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)
- የጨረታ ማስከበርያ በድርጅታችን “የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር” ስም በአዋሽ ባንክ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር ሲ.ፒ.ኦ አሰርተው ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ፋይናንሻል ዶክመንት በፖስታ አሽገው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን ከኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እርዳታና ልማት ማህበር ግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
- ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ የሆኑት ዕቃውን በአንድ ሳምንት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
- ለሽሮ እህል እና ለምስር ክክ ሩብ ኪሎ ሳምፕል ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀሙስ ጥር 26/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0949231127 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ማሳሰቢያ፡- አትክልት ያሸነፈው ድርጅት በየ15 ቀኑ ለ2 ወራት ያለምንም ዋጋ ለውጥ ኬላ እና ቡራዩ በሚገኘው የምገባ ማእከላችን አትከልቱን ማቅረብ ይኖርበታል።
የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን
የእርዳታና ልማት ማህበር
