ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ንብረቶችን በመንግስት ግዢና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 አንቀጽ 59 መመሪያ በሚያዘው መነሻ መሰረት ባገለገሉ ንብረት ክፍል ውስጥ በግቢ እድሳት የተሰበሰቡ ጎረንዳዮ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ንብረቶችን በመንግስት ግዢና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 አንቀጽ 59 መመሪያ በሚያዘው መነሻ መሰረት ባገለገሉ ንብረት ክፍል ውስጥ በግቢ እድሳት የተሰበሰቡ ጎረንዳዮ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መነሻ መሰረት
- በግቢው እድሳት የተሰበሰቡ ጎረንዳዮ ብዛት ያላቸው አንድ ላይ የተሰበሰቡ በግምት ብዛቱ 950 ኪ.ግ ሲሆን የጨረታው መነሻ ዋጋ ብር 52,250.00 (ሃምሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ነው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) ነው፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን የያዘውን የጨረታ ሰነድ በመሸጫ ዋጋ 50 ብር ሲሆን ሁሉም ተወዳዳሪ ከመወዳደሩ በፊት ንብረቱን ያለበት ቦታ በአካል በመሄድ ካያችሁ በኋላ ለመጫረት የፈለጋችሁ ተጫራቾች በመንግስት ግዢና አስተዳደር ዳይሬከቶሬት በአካል በመምጣት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት በኮሌጁ የግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይቻላል። የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ8ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ (በአመች ቦታ) ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በስራ ቀን ያልዋለ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተገለጸው መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከኦሪጅና የጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች በ5 ቀን ውስጥ ክፍያውን ፈፅሞ ከላይ የተጠቀሱትን ንብረቶች መውሰድ አለበት፤ ስለሆነም ተጫራቹ በጨረታው ተሸናፊ ከሆነ ያስያዘው ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመሳሽ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ኮሌጁ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ኢስት አፍሪካ ቦትሊግ አክሲዮን ማህበር ኮካ ኮሳ ፋብሪካ አጠገብ፡፡
ስልክ ቁጥር ፡- 011-2-73-64-94
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
