በአዲስ አበባ በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ያሉትን እቃዎች እነዚህም ፡- ሎት1 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 2 የስፖርት ዕቃ፤ ሎት 3 የስቴሽነሪ እቃ፤ ሎት 4 የቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 002/2017
በአዲስ አበባ በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ያሉትን እቃዎች እነዚህም ፡- ሎት1 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 2 የስፖርት ዕቃ፤ ሎት 3 የስቴሽነሪ እቃ፤ ሎት 4 የቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሆን አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመከፈላችሁ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፤
- በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የምዝገባና ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማቅረብ አለባችሁ።
የሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ብር
ሎት 1 የፅዳት እቃዎች ብር 1000
ሎት 2 የስፖርት ዕቃዎች ብር 1000
ሎት 3 የስቴሽነሪ እቃዎች ብር 1000
ሎት 4 የቋሚ እቃዎች ብር 1500
- የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን 14/5/2017 ዓ.ም በየሎቱ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ፋይናንስ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚጠናቀቅበት ቀን 27/5/17 ዓ.ም በ10፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የግዥ ቢሮ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥኑን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል ናሙና ማቅረብ ለማይቻልባቸው ፎቶ ወይም ብሮሸር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፈበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ንብረት ከፍል ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20 በመቶ የመቀነስ ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- 22 ዘሪሁን ህንፃ 100 ሜትር ገባ ብሎ በተለምዶ ሚኪሊላንድ ጎዳና
ለበለጠ መረጃ ፡- 0116 66 39 76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር
ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ 2ኛ ደ/ት/ቤት
