በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 ዓመት አገልግሎት የሚውል ኦርጅናል አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የትምህርት እቃዎች፣ ህትመቶች እና ቋሚ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 ዓመት አገልግሎት የሚውል ኦርጅናል አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የትምህርት እቃዎች፣ ህትመቶች እና ቋሚ ዕቃዎች ለመግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ ቲን-ነምበር እና አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ አለባቸው::
- ተጫራቶች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ዕንቁላል ፋብሪካ እምብልታ ሆቴል ከፍ ብሎ ከሚገኘው የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎችን ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማችሁን፣ ፊርማችሁን አድራሻችሁን ማስፈርና ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት በጄኔራል ታደሰ ብሩ iኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት1 የአላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር) ለሎት 2 የፅዳት እቃዎች ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር) ለሎት 3 የደንብ ልብስ ብር 1000 (እንድ ሺህ ብር) ለሎት 4 የትምህርት እቃዎች ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር) ለሎት3 ህትመቶች ብር 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ለሎት 6 የደንብ ልብስ ስፈት ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ለሎት7 ቋሚ እቃዎች ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው::
- መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም 20% ከውሉ በፊት መቀነስ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ እስከ 6 ወር ዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ ተጨማሪ 25% ዕቃ ግዥ መፈፀም ይችላል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ ያሸነፈውን እቃ የመ/ቤታችን ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አምጥቶ ማስረከብ አለበት፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ በነጻ የሚወስዱትና የጨረታ ማስከበሪያ በደብዳቤ የሚያስገቡት በራሳቸው ምርት ባመረቱት ብቻ ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118278952
በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት
