Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Steel Pipe Mill PLC (OSPM) (የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃ.የተ.የግ.ማ)
  • Address ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ብትወደድ ባህሩ ህንጻ 3ኛ ወለል : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115522681
  • Websitehttps://oromiasteelpipemill.com/wp/
  • Deadline28 Feb 2025, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories

ፋብሪካችን የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ

 

ፋብሪካችን የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች ግለሰቦች ማስረጃቸውን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኩባንያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ የካቲተ 21 ቀን 2017 . ከቀኑ 500 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው: ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 530 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎ ግራም የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት /ቤት ፊት ለፊት ብትወደድ ባህሩ ህንጻ 3 ወለል በሚገኘው የኩባንያው /ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡

የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸው ትራንስፖርት በማቅረብ ተረፈ-ብረቶቹን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን ጥሬ ዕቃ የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያችን ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል፡፡ ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፣ 251-5522681/ 251-5522731

አዲስ አበባ

 

የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ

 

Save Tender