የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዓይነት ሎት 1 - የፈርኒቸር ዕቃዎች እና ሎት 2 - የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዓይነት
ሎት 1 - የፈርኒቸር ዕቃዎች
ሎት 2 - የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ፡-
1ኛ በመስክ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2ኛ ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
3ኛ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት
4ኛ የእቃ አቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው ድርጅቶች በሐድያ ዞን ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀው
የጨረታ ሰነድ ብር ሎት 1፣ 200 /ሁለት መቶ ብር ሎት 2፣ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
ሎት 1 ፡- 300 ብር
ሎች 2 ፡- 30,000 ብር
በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ የመወዳደሪ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0461784281/0465552337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
