በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በዓመቱ በተለያየ ወቅት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች ለሠልጣኞች አገልግሎት የሚሰጥ የዳቦ ማሽን እና የዳቦ ፓትራዎችን ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል፤
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር AAPPC 004/17
በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በዓመቱ በተለያየ ወቅት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች ለሠልጣኞች አገልግሎት የሚሰጥ ፡-
- ሎት 1 የዳቦ ማሽን 80X100 የሆነ የጣሊያን ስሪት በኤሌክትሪክ የሚሠራ አጠቃላይ ሰርቪስ ሥራ፤
- ሎት 2 የዳቦ ፖትራ /Flat Aluminum Tray 80cm X 100cm X 3cm, Thickness 1.0/ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
በመሆኑም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥ አዋጅ በተገለፀው ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይፈጸማል፤ በኤሌክትሪክ የሚሠራ የጣሊያን ስሪት የዳቦ ማሽን ሙሉ ሰርቪስ እና የዳቦ ፓትራ ጨረታው የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ /Tax clearance/ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም ተ.ኢታ /VAT/ ሰርተፊኬት እና ቲን /TIN/ ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ ይሆናል፤ በሁሉም ሎቶች ላይ የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የሚያቀርቡት ሰነድ በአጠቃላይ የታደሰ መሆን አለበት።
* ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 28 በሥራ ቀናት ቅዳሜና እሁድን እንዲሁም የበዓላት ቀናትን ጨምሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበት የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል። ከአደራጃቸው አካል በሚጫረቱበት ሎት በዘርፉ መሰማራታቸውን የሚገልፅ የቅርብ ጊዜ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው::
* ተጫራቶች ለሎት 1. ብር 8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር/ እና ለሎት 2. ብር 5.000.00 /አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ስም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
* ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ቅዳሜ፣ እሁድን እንዲሁም የበዓል ቀናትን ጨምሮ የኮሌጁ ፋይናንስና ግዥ ዲቪዚዮን በመቅረብ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሁለት ፖስታ ፋይናንሺያል ኮፒና ኦሪጅናል እንዲሁም በሁለት ፖስታ ቴክኒካል ኮፒና ኦሪጂናል በድምሩ በ4 ፖስታ ሰነዶችን በመለየት ማስገባት አለባቸው::
* ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፤ የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጁ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፤ የመዝጊያውና የመክፈቻው ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ሳይሆን ቀርቶ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
* ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን እንደ የመልካም ሥራ አፈፃፀም እና የመሳሰሉትን ማቅረብ የተሻለ ውጤት አለው።
* መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ኮልፌ ሉኳንዳ አዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ / የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ/ አጠገብ፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0112-73 -94-86፣ 0112-73-95-48 ወይም +251-118-33-38-45
በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ
