በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል ።
የብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር እ.አ.ስ.ስ.አ.ኮ.ስ.ማ 002/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፤ ስለሆነም፡-
ሎት 1፡- የምግብ ዝግጅት ግብዓቶች፤
ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች፤
ሎት 3፡- አላቂ የጽዳት እቃዎች
ሎት 4፡- የምግብ ማብሰያና ተጓዳኝ እቃዎች፣
ሎት 5፡- የኤሌክትሮኒክስ እና ተጓዳኝ እቃዎች፤
ሎት 6፡- የፋይር ኤክስቲንጉሽር መሣሪያዎች፤
ሎት 7፡- የጅም መስሪያ መሣሪያዎች፤
ሎት 8፡- የፈርኒቸር እቃዎች፤
ሎት 9፡- ጀነሬተር እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና ሲሆኑ
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ምስክር ወረቀት፣ ግብር ከፋይነትን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት (ታክስ ክሊራንስ) እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር /በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ድረስ ብቻ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላል::
- ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ሥልጠና ማዕከሉ ግዥ ክፍል ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሥልጠና ማዕከሉ ትንሹ አዳራሽ ይከፈታል። እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ፋይናንሻል (የዋጋ መወዳዳደሪያ) ፖስታው የሚከፈትበት ቀን በደብዳቤ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል ስም የተዘጋጀ የገንዘብ መጠን ለእያንዳንዱ ሎት በተናጠል ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሽያል ሰነዶች ተለይተው በተለያየ ፖስታ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ በአራት (4) ፖስታ በማድረግ ኮፒ እና ኦርጅናሉ በጉልህ ተጽፎ መቅረብ ይኖርበታል፤ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር መቅረብ አለበት::
- ናሙና (sample) ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በክፍል 6 በተጠቀሰው መሰረት ጨረታው ከመዘጋቱ ከ 11 ኛው ቀን 4፡00 በፊት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ስታዲየም ጎን ነው
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 888 9336/011 434 0616 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ::
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል
