ፋብሪካችን ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለ4ኛ ጊዜ የወጣ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጣበስፋ/ያዕሽ/ ብግጨ/10/2017
ፋብሪካችን
በሎት-1 የተለያዩ መጠን ያላቸው STAINLESS STEEL PIPE
በሎት-2 የተለያዩ መጠን ያላቸው INDUSTRIAL SHADE STRUCTURE STEEL
በሎት-3 የተለያዩ መጠን ያላቸው VALVES እና
በሎት-4 የተለያዩ መጠን ያላቸው ELECTRICAL POWER CABLE
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 ላይ በተገለፀው አድራሻ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶሰት መቶ ብር/ ብቻ በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000057735167 ገቢ በማድረግ ከታች በተመለከተው አድራሻ ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከምሳ በኋላ ከ7:00-11:00 ሰዓት ቅዳሜ ከ2:00 እስከ 6:00) መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንስ ሆስፒታል አካባቢ
የፌደራል ቤቶች ኮርፖረሽን ህንጻ፡ :
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 5-586725 /0912031748
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% /ሁለት ከመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም ለ3 ወራት የሚያገለግል በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጋራንቲ (ቢድ ቦንድ) በጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች የሚገኙበት አድራሻ አማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ግቢ ውስጥ ነው::
- በጨረታው ተሳትፎ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ከፋብሪካው ጋር ውል በመያዝ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ሙሉ ክፍያ ቅድሚያ ከፍሎ ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
