በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለሰብል ልማት ዳይሬከቶሬት ለደሴ አፈር ምርመራ ላብራቶሪ እና ለባህርዳር አፈር ምርምር ላብራቶሪ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የላብራቶሪ ቁሳቁስና መለዋወጫ ሎት 2 የድንጋይ ከሰል መፍጫ ማሽን ሎት 3 የህያው ማዳበሪያ ማሽን እስፔርፓርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 8
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለሰብል ልማት ዳይሬከቶሬት ለደሴ አፈር ምርመራ ላብራቶሪ እና ለባህርዳር አፈር ምርምር ላብራቶሪ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የላብራቶሪ ቁሳቁስና መለዋወጫ ሎት 2 የድንጋይ ከሰል መፍጫ ማሽን ሎት 3 የህያው ማዳበሪያ ማሽን እስፔርፓርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከአርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 500.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ገንዘብ የዋጋውን ጠቅላላ ድምር ከ0.5% /ፐርሰንት/ ያላነሰ እና ከ2% ያልበለጠ ሲፒኦ አሰርተው፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ እና በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ስም በመሂ.1. ገቢ አድርገው የደረሰኙን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 25 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የመጀመሪያ ሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ የለበትም ነገር ግን ካልቀረበ ይዞት የቀረበውን ናሙና ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 3208095/0582205849/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በተሞላው ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ በፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡ የጥቅል ዋጋው ከነጠላ ዋጋው በሚለያይበት ጊዜ በነጠላ ዋጋው ስሌት ይወሰዳል፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
