የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ለሚሰራቸው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና የመንገድ ጥገና ሥራዎች አገልግሎት የሚውል የግንባታ ፌሮ ብረት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/- 06/17
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ለሚሰራቸው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና የመንገድ ጥገና ሥራዎች አገልግሎት የሚውል የግንባታ ፌሮ ብረት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
በመሆኑም፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የመንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀትና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ዋና እና አንድ ኮፒ የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ዋና እና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ለሁሉም የብረት ዓይነቶች ብር 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/ ብቻ በማሠራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
የስልክ ቁጥር +251 113 659932
ወልቂጤ- ኢትዮጵያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
