በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልገሎት የሚውሉ፡- 1. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ 2. የፅዳት ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልገሎት የሚውሉ፡- 1. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ 2. የፅዳት ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም ሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1054551161211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል አዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኮፒና ኦርጂናሉን ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ አለበት። ቴክኒካሉን ያለፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻላቸው ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ውስጥ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- ማንኛውም የእስቴሽነሪ እና የጽዳት እቃዎች ተወዳዳሪዎች ሳፕል ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ አዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀው በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት፣ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሽናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት ያሸነፈበትን ዕቃ ብዛት አብዝቶ የጠቅላላውን ዋጋ 10% የውል ዋስትና ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን ፣ 7.5 % በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር-022-211-14-42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
