የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2017 በጀት አመት አካል ጉዳተኞች በልብስ ስፌትና የፀጉር ስራ የስራ ዘርፍ ወደስራ እንዲገቡ የተለያዩ ለስራው የሚያስፈጉ ግብዓቶች ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ (04/001-002/2017)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2017 በጀት አመት አካል ጉዳተኞች በልብስ ስፌትና የፀጉር ስራ የስራ ዘርፍ ወደስራ እንዲገቡ የተለያዩ ለስራው የሚያስፈጉ ግብዓቶች ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ / አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
የልብስ፤ የቆዳ መስፊያ ማሽንና የተለያዩ የቆዳ ስራ የሚያስፈልጉ እቃዎች ግዥ |
100,000.00 CPO |
|
ሎት 2 |
ለሴትና ለወንድ ፀጉር ስራ የሚያስፈልጉ እቃዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
20,000.00 CPO |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቶች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በቢሮ አካውንት 1000009650559 በማስገባት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከቢሮው ከፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ደረሰኝ በማስቆረጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው እና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ ኮፒና ዋና (ኦርጅናል) ሰነድ ብለው በ2 ፖስታ በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ታሽጐ በእለቱ 4፡30 ሰዓት በቢሮው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ነው::
- ተጫራቶች ናሙና ለሚጠየቅባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ ፡- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል ፡፡
አድራሻ ፡- አ/አ/ከ/ሴ /ህ/ማ/ጉ/ቢሮ ደጃች ውቤ ከጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ወደ አፍጮ በር አደባባይ በሚወስደው መንገድ የስድስት ኪሎ የፈረንሳይ ታክሲ መጫኛ አለፍ ብሎ ቢሮ ቁጥር 206 1888 ህንፃ ላይ 2ኛ ፎቅ ስ.ቁጥር 09 47 95 17 60/09 42 12 94 92
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ
