የኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር የህንፃ መሳሪያዎች እና ያገለገሉ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር የህንፃ መሳሪያዎች እና ያገለገሉ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፤
- ደብረዘይትመንድሳሪስ ከሚገኘው የድርጅቱ ሽያጭ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10:00 ሰዓት ብቻ ነው።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሁኔታ እስከ ጨረታው መዝጊያ ጊዜ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00-10፡30 ድረስ አክሲዮን ማህበሩ ንብረት ክፍል ውስጥ በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያቀረቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ ተካቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታው መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 011 442 3659 በመደወል መረዳት ይቻላል
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር
