በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰብ ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያዎችና ግዴታዎችን ማሟላት አለባቸው።
የጨረታ መመሪያ
- ዕቃዎቹን ለመግዛት የሚጫረቱ በሰነዱ ላይ በተመለከተው ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000.00 በሲፒኦ ( በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት)።
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር መክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እያንዳንዱ ያገለገሉ ዕቃዎች ዋጋ በማስቀመጥ በታሽገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡
- የሚሸጡ እቃዎች ዝርዝር ሁኔታ ሁልጊዜ በስራ ሰዓት ሀዋሳ ቶጋ በመከላከያ ካምፕ በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ዕቃዎቹን በ5 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አጠቃልሎ ማነሳት አለበት።
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ዕቃዎቹን አጠቃሎ ካላነሳ በየቀኑ 1% ብር ቅጣት ይከፈላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 200ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ባሉት ቀናት ውስጥ ቶጋ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሀዋሳ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቶጋ ካምፕ ብሪፈንግ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡40 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ድርጅቶችም ሆነ ግለሰብ ውል ሲፈፅሙ ያሸነፉበትን ዋጋ ወደ ደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በፋይናንስ ቡድን ስም በተከፈተው አካውንት ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር፡-09 01 99 73 01/ 09 21 06 32 80 ይደውሉ
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
(ሀዋሳ ቶጋ ካምፕ)
